Copy
ባልጸና ጎጆ- የጸና ብርታት
በማርታ ታደሰ
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ በአመቱ በሚከሰቱ ጎርፎች ከፍተኛ ጉዳት ከሚደርስባቸው ክልሎች አንደኛው ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጦች እና ከመሬት አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ምክንያቶች በመንስኤነት እንደሚጠቀሱ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡ ጎርፍ የሰብል ውድመት የሚያስከትል በመኾኑ፤ ይህም የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግርም እንዲከሰት ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል result ፡፡ በ2020 በክልሉ በጎርፍ የተነሳ 11.749 ሰዎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው ህይወታቸው ሊመሳቀል ችሏል፡፡
 ጋምቤላ የአቹዋ ቀበሌ 
ሙሉውን ታሪክ በ InfoNile ላይ ያንብቡ
በጋምቤላ ባሮ-አኮቦ-ሶባት ከፊል ተፋሰስ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ይጋሩታል፡፡ ዋንኞቹ ወንዞችም ባሮ፣ አኮቦ እና ፒቦር ናቸው፡፡ የባሮ ወንዝ ከአኮቦ እና ፒቦር ጋር ከተገናኘ በኋላ፤ ወደ ባህሬል ጀቤልን ለመቀላቀል ወደ ሰሜን ምዕራብ የሚፈሰውን ሶባትን ይፈጥራል፡፡ በሒደትም ነጩ አባይን ይፈጥራሉ፡፡
ባሮ-አኮቦ-ሶባት ንዑስ ተፋሰስ
ባሮ-አኮቦ በኢትዮጵያ በትልቅነቱ በአራተኛነት የሚጠቀስ ተፋሰስ ቢሆንም የሚገባውን ያህል መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ያልሆነ እና የተሰነደ በቂ መረጃ የሌለው ነው፡፡ በአብዛኛው በአባይ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች ትኩረታቸው በአባይና በተከዜ ተፋሰስ ዙሪያ ነው፡፡  

ባለፈው በ2021 አመት ግንቦት ወር ላይ ወደ ጋምቤላ ክልል ኦታን ወረዳ ተጉዤ ነበር፡፡ የጉዞዬ አላማም በየአመቱ በሚከሰት ጎርፍ የሚፈናቀሉ፤ ደግሞም የጎርፉ ወቅት ሲያልፍ ወደ መኖሪያ ቀዬአቸው ለመመለስ የሚጓዙ ሰዎችን ታሪኮች በምስል ለመያዝና ለመስራት ነበር፡፡ እናም ይህ “አሁንም ድረስ መኖሪያ ነው” የተሰኘው ታሪክ የሰብአዊነት ታሪክ ነው፡፡ የሰዎች ጽናት ጥንካሬ ታሪክ ነው፡፡

ትኩረት ያጣው ትልቁ ሐብት

የመቱ ዩኒቨርስቲ በ2013 ላይ ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት ላይ study ባሮ-አኮቦ ተፋሰስ የተዘነጋ ሐብት መሆኑን ያመለክታል፡፡ “በኢትዮጵያ ካሉ 12 የወንዝ ተፋሰሶች መካከል ባሮ-አኮቦ ተፋሰስ ከፍተኛ የውሀ ሐብቶች ያለው፤ ግን ደግሞ እስከ አሁን ድረስም ምንም አይነት የማሻሻያ ልማት ያልተደረገለት ነው፡፡ የባሮ-አኮቦ ተፋሰስ ትኩረት ያልተሰጠው ታላቅ አቅም ያለው፣ በኢትዮጵያ መመዘኛዎች አነስተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚገኝበት እና በርካታ የመሬትና የውሀ ይዞታ ያለው ነው፡፡”

ወንዙ በአካባቢው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ዋንኛ የውሀ ማግኛ ምንጫቸው ሆኖ ያገለግላቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎችም ጎርፍ ሲያልፍ ጠብቀው ማሽላ፣ በቆሎና አትክልቶችን ለማምረት የሚተጉ፤ እንዲሁም በእንስሳትና አሳ ምርት ላይ ጥገኛ የሆኑ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡

ይሁንና እስከ 12 ሳምንት የሚቆየውና በየአመቱ የሚከሰተው ጎርፍ በአካባቢው መጠነ ሰፊ የሆነ ጉዳትና መፈናቀልን አድርሷል፡፡ በ2014 ላይ 42.000 ሰዎች በሚኖሩበት ኡታንግ ወረዳ ያሉ 95 በመቶ የሚሆኑ ቀበሌዎች በወንዝ ደለል ቀጠናዎች ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ (UNECA) መረጃ report ያመለክታል፡፡
መንደሮችን የሚያጥለቀልቀው ጎርፍ በሽታዎችንም የሚያስከትልና በሰብል ምርት ወቅት የሚከሰት በመሆኑ ለምግብ ዋስትና ችግርም መዳረጉን CGIAR የተባለው አለምአቀፍ የግብርና ምርምር አማካሪ ቡድን የሰራው ጥናት ውጤት reported ያሳያል፡፡
Read in English
በሴፕቴምበር 2020 መጨረሻ በኢትዮጵያ ክልሎች በጎርፍ የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር

አሳ አጥማጆቹ

በ2014 ይፋ በሆነ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የውሀ አካላት በየአመቱ አሳ የማምረት አቅም /fishery production/ 94.500 ቶን ያህል እንደሚገመት ነው፡፡ ይሁንና በትክክል የተገኘው የምርት መጠን 38.370 ቶን ነው፡፡ 

አሳ ለኢትዮጵያኖች በተለይም ደግሞ በባሮ ወንዝ፣ ጣና ሀይቅ፣ ዝዋይና በሌሎችም የውሀ አካላት አቅራቢያ ለሚገኙ ነዋሪዎች ዋንኛ የፕሮቲን መገኛ ምንጭ major protein source ነው፡፡ 

በኢትዮጵያ ትልቅ የሆነ የአሳ ማምረት አቅም ቢኖርም የሚገኘው የምርት መጠን ግን አሁንም ድረስ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ የማምረት ተግባሩም በዘመናዊ ሰው ሰራሽ የአሳ ማርባት ሳይኾን በባህላዊ መንገዶች ላይ ጥገኛ ነው፡፡ በቂ ያልሆነ የአሳ ማጥመጃ እቃዎች፣ ያልዘመነ የመጓጓዣ አቅርቦት፤ ከምርት በኋላም ደካማ የምርት አያያዝ፤ የመሸጫ ዋጋ ማነስ እና ምቹ ያልሆነ የገበያ ቦታ ተጠቃሽ የሆኑ ተግዳሮቶች include እንደሆኑ በ2020 ይፋ የሆነው ጥናት አስረድቷል፡፡

ኦማን ኦካቺ እና ኦሞት ኦሞት የ27 እና የ25 አመት ወጣቶች ሲኾኑ፤ በአቹዋ ቀበሌ በወንዝ አቅራቢያ ነው ተወልደው ያደጉት፡፡ ኦሞት የአሳ ማጥመድ ስራውን ከጀመረ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ኦማን ደግሞ በዘርፉ ለ10 አመታት ሰርቷል፡፡ ሁለቱም ኑሯቸውን የመሰረቱት ሙሉ በሙሉ በአሳ ማጥመድ ላይ በመኾኑ፤ በአካባቢው የጎርፍ ወቅት ሲመጣ ስራቸው ላይም አሉታዊ ተጽዕኖን ፈጥሮባቸዋል፡፡ ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ባሉት ጊዜያት ስራቸውን መስራት አይችሉም፡፡ ኦማን እና ኦሞት በጠዋት የአሳ ስራቸው ላይ ተሰማርተው ይታያሉ፡፡

ኦሞት ኦሞት የአሳ እርባታ ስራውን ከሶስት አመታ በፊት ማህበር በመቀላቀል ነው ስራውን የጀመረው

“ያደኩት ወንዝ አጠገብ በመሆኑ ጀልባን እንዴት እንደምጠቀም መማር ችያለሁ፡፡ በጀልባችን የአካባቢውን ህብረተሰብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ያለ ክፍያ እናጓጉዛለን፡፡ የአሳ እርባታ ማህበር አባል ነኝ፡፡ ማህበራችን ሁለት ጀልባዎች አሉት፡፡ ህብረተሰቡን ለማጓጓዝም ሆነ ለራሳችን የአሳ ማጥመድ ስራ እንጠቀምባቸዋን” ይላል፡፡

ሙሉውን ታሪክ በ InfoNile ላይ ያንብቡ
ኦማን ኦካቺ እና ኦሞት ኦሞት 7 ኪሎ ግራም የሚመዝን የናይል ፐርች አሳን ወደ ጋምቤላ ከተማ ለመውሰድ ወደ መጓጓዣ መናኸሪያ እየተጓዙ ነበር፡፡ ቲላፒያ፣ ጊል ፊሽ፣ ለን ፊሽ እና ናይል ፐርች በዚህ አካባቢ የሚገኙ አራት የአሳ አይነቶች ናቸው፡፡ አብዛኛው የናይል ፐርች አሳ የሚሸጠው ጋምቤላ ከተማ ነው፡፡ ቀሪዎቹ  የአሳ አይነቶች ደግሞ በአካባቢው በሚገኘው ገበያ ለማህበረሰቡ ይሸጣሉ፡፡ አንድ ናይል ፐርች አሳ ዋጋ ወደ 200 ብር አካባቢ ነው፡፡ 

አረቄ አውጪዎቹ

አጉዋ ኦጋላ የ30 አመት ወጣት ስትኾን፤ በባሮ ወንዝ አቅራቢያ በአቹዋ ቀበሌ ነው የተወለደችው፡፡ የባሮ ወንዝ ውሀን ለመጠጥ፣ ለእርሻ፣ ለአሳ እና የአረቄ መጠጥን ለመስራት ትጠቀምበታለች፡፡ ይሁንና በአቹዋ ቀበሌ እንደሚኖሩ ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች በየአመቱ ከሰኔ እስከ ሐምሌ ባሉት ጊዜያት እሷና ቤተሰቧ የጎርፍ አደጋ ይገጥማቸዋል፡፡

አጉዋ እንደምትናገረው ጎርፍ በሚከሰት ጊዜም ቤተሰቧ ጊዜያዊ የመኝታ አልጋዎችን በማዘጋጀት ውሀ ላይ ይተኛሉ፡፡ ጎርፍ እንደ ወባ እና ጉንፋን ላሉ የተለያዩ በሽታዎች እንዳጋለጣቸውም ትናገራለች፡፡ 

አጉዋ ኦጋላ በእርሻ ቦታዋ ላይ ሆና ትታያለች፡፡ ምንም እንኳን ጎርፍ ፈተና ቢሆንባትም ከመንደሯ ርቃ የመሔድ እቅድ የላትም

አጂሉ ኦሌሮ የ40 አመት ጎልማሳ ስትኾን፤ በባሮ ወንዝ አቅራቢያ በአቹዋ ቀበሌ ነው የምትኖረው፡፡ ለ25 አመታት ያህል አረቄ ስትሸጥ ቆይታለች፡፡ 

አጂሉ በቀን ሁለት ጊዜ 300 ሊትር ውሀን ከወንዙ ትቀዳለች፡፡ ዋንኛ የገቢ ምንጭዋ ወንዙ ነው፡፡ በአቹዋ ቀበሌ እንደሚገኙ እንደ ሌሎቹ የህብረተሰብ ክፍሎች እሷም የጎርፍ ወቅት ሲመጣ ስራዋን ታቆማለች፡፡ 

አጂሉ ኦሌሮ ከወንዙ አቅራቢያ የአረቄ መጠጥን ታዘጋጃለች
አጂሊ በባሮ ወንዝ ውሀ ከጠመቀችው አረቄ በጠርሙስ ጋር

አርሶ አደሮቹ

የ40 አመት እድሜ ያላት አሪየት አባይ ከስድስት ልጆቿና ባለቤቷ ጋር በአቹዋ ቀበሌ ከባሮ ወንዝ አጠገብ ነው የምትኖረው፡፡ ቤተሰቦቿን የምትረዳው ባህላዊ የአሳ ማጥመድ መንገዶችን በመጠቀም በምታገኘው ገቢ ሲኾን፤ የበቆሎ እርሻም አላት፡፡ የጎርፍ ወቅት ቤተሰቧ ከነእቃቸው ወደ ሌላ አቅራቢያ መንደሮች በመሔድ ከዘመዶቻቸው ጋር ከሁለት እስከ ሶስት ወራት ድረስ ይኖራሉ፡፡

አሪየት አባይ ቲላፒያ አሳን በኩሽናዋ ውስጥ ታዘጋጃለች፡፡ ቲላፒያ አሳ በባህላዊ መንገድ ከምታጠምዳቸው አሳዎች መካከል አንደኛው የአሳ አይነት ነው፡፡

Read in English

አርሶ አደር ኡጁሉ ኦማት በአቦል ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ደጅ ከወንዙ ፊት ለፊት ቆሟል፡፡ ለእርሻ ስራ ከፒንኬው ቀበሌ ወደ ባሮ ወንዝ ለመስፈር ተገዷል፡፡ ከወንዙ አጠገብም የበቆሎ እርሻ አለው፡፡

ከባሮ ወንዝ አጠገብ መኖር ለኡጁሉ እና ለቤተሰቡ የውሀ አቅርቦት እንዲኖራቸው ቢያደርግም፤ መደበኛው ጎርፍ ክስተት ግን የማይቀር ፈተና መሆኑ አልቀረም፡፡ ብዙ ጊዜም እርሻው በጎርፍ ወድሞበታል፡፡ እናም ዝናብን ለመጠባበቅ ወደ ትውልድ መንደሩ ተመልሷል፡፡ ይሁንና እንደ ብዙዎቹ ጎረቤቶቹ ሁሉ ኡጁሉም ጎርፉ ሲያልፍ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ወደ ባሮ ተመልሶ ይመጣል፡፡

በ InfoNile ላይ ተጨማሪ ታሪኮችን ያንብቡ
ይህ የኤቭሪዴይናይል #EverydayNileዘገባ በኢንፎናይል ከአይኤችኢ- ዴልፍት አለምአቀፍ ትብብር ለውሀ እና ለልማት ተቋም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ አርትኦት አኒካ ማክጊኒስ፤ ዳታ ቪዥዋላይዜሽን ሩት ምዊዜሪ እና ግራፊክስ ጆናታን ካቡጎ ተሳፈውበታል፡፡
በ#Everyday ናይል ላይ ተጨማሪ ታሪኮችን ያንብቡ
WORKSHOP TRAINING
Apply Here
Share Share
Tweet Tweet
Forward to a friend Forward to a friend
Facebook
Twitter
Link
Website






This email was sent to <<Email Address>>
why did I get this?    unsubscribe from this list    update subscription preferences
InfoNile.org · 5th Street Industrial Area PO Box 7381, Kampala UGANDA · Kampala · Uganda